30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ

Huda Soft
تنزيل 30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ APK
تقييم 4
الفئة الكتب والمراجع
اسم الحزمة qissa.sohaba.hudasoft
عمليات التثبيت 5+
لمحة عن 30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ
በአላህ ስም በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው
የአላህ ሰላትና ሰላም ከፍጡራን ሁሉ ምርጥ በሆኑት በነብያችን (ﷺ) ላይ ይውረድ።

ይህ አፕ ምርጥ የሆኑትን የነብያችን ﷺ ባልደረቦች ታሪክ በአጭሩ አካቶ ይዟል።
ሶሀቦች ቁርአንን የህይወታቸው ብርሀን አድርገው ይዘውታል። የኢስላምን መርሆችና አስተምህሮቶች ወደ ህይወት ለውጠዋል። በስነ ምግባር ምጥቀት ስፋትና በአላማ ፅናት እንዲሁም በመልካም ስብዕና ከፍተኛ ደረጃ ለመድረስ በቅተዋል።
ነብዩም (ﷺ) እንዲህ ሲሉ አወድሰዋቸዋል
"ከሁሉም ምርጡ ትውልድ እኔ የምገኝበት ትውልድ ነው ፣ ከዚያም የሚቀጥለው ፣ ከዚያም የሚቀጥለው ፣ ከዚያም የሚቀጥለው ..."
ታላቁ ሶሀባ ዐብደላህ ዒብነ መስዑድ የሶሀቦችን ገድል በዘከሩበት ንግግራቸው እንዲህ ይሉናል ፦
"አረአያ ሊሆን የሚችል ስብዕና የሚሻ ካለ የመልዕክተኛው ባልደረቦች ብቻ ናቸው አርአያ ሊሆኑ የሚችሉት እናም የሶሀባ ትውልድ አባላት። ምክንያቲም እነሱ ከማንም በላቀ ሁኔታ የጠለቀ ዕውቀት ባለሀብቶች ነበሩና። ቀጥተኛውን ጎዳና መርተዋል። አላህ ለመልእክተኛው ባልደረባነት አጭቷቸዋል የዚህን ዲን ታላቅ አደራ ተሸክመዋል። ማንነታቸውን እወቁ ፣ ፈለጋቸውንም አደራ ተሸክመዋል። ማንነታቸውን እወቁ ፣ ፈለጋቸውንም ቀጥተኛውን የህይወት መንገድ የተከተሉ ሰወች ነበሩና።
በየትኛውም ቦታና ጊዜ የምንገኝ ሙስሊሞች የዚያ ድንቅ ትውልድ ፤ የዚያ ቁርአናዊ ማህበረሰብ አባላት አርአያነት እንደሚያስፈልገን ግልፅ ነው።ከሶሀባ ትውልድ ታሪክ በጣም ብዙ እንማራለን።ከምርጥ ስብእናቸው የጠራ ምንጭ እንጎነጫለን። በህይወት ውስጥ ያደረጉት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ለህይወት ጉዟችን ብርሀን ነው። የማንነታችን መለያ ነው… "።ከቀደምቶች ታሪክ እራሳችንን እንድናስተምር ይህ የሶሀበች ታሪክ የሚለው አፕ አስተማሪ ይሆናል ብለን እናስባለን።
በዚህ አፕ ታሪካቸው ያልተጠቀሱ ብዙ ሶሀቦች አሉ ፤ በአላህ ፍቃድ በየግዜው የሌሎችም ሶሀቦች ታሪኮችን አካተን አፑን በየግዜው እናድሰዋለን ፣ ከእርሶ የሚጠበቀው ይህን አፕ በየግዜው ማዘመን / تحديث ማድረግ ነው።

ከአጅሩ ተቋዳሽ ይሆኑ ዘንድ አንብበው ለሌሎችም ያጋሩ።

ይህ ስራችን የተከበረው የአላህን ፊት ተፈልጎበት የተሰራ እንዲሆን እንዲሁም ታሪኩን ከተለያዩ ምንጮች ላሰባሰቡ ፀሐፊዋች ለኛም በዚህ ስራ ለተባበሩንም በሞት ለተለዩንም ይህንን ስራ ለሚያሰራጩትም ይቀበለን ይቀበለን አላህን እማፀነዋለሁ

በአላህ ፍቃድ ሌሎች ጠቃሚ አፖችን አዘጋጅተን በቀጣይ እናደርሳችኃለን።
________________
የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል - ከናንተ ውስጥ መጥፎን ነገር ያየ በእጁ ይቀይር ካልቻለ በምላሱ ካልቻለ ደግሞ በልቡ ይጥላ ይህ ግን (በልብ ብቻ መጥላት) ደካማ ኢማን ነው "(ሙስሊም ዘግበውታል)
ወንድም እህቶቼ ታሪኩን በምታነቡበት ግዜ ከቁርአን ከሀዲስ የተጨመረ ወይም የተቀነሰ ነገር ካገኛችሁ በአድራሻዬ አድርሱኝ።
ስህተቴን ላረመኝ ሰው አላህ ይዘንለት።

አላህ ሆይ! ጠቃሚ እውቀትን ከተግባር ጋር ወፍቀን መጨረሻችንንም አሳምርልን አሚን! ከተሳሰትኩ ከነፍስያዬና ከሸይጧን ሲሆን ሐቅን ከገጠምኩኝ ከአላህ ﷻ ነው።

የአፑ አዘጋጅ አብዱራሂም ማህሙድ

※ ከዚህ በፊት ያዘጋጀነውን የነብያት ታሪክ አፕ በሚከተለው ሊንክ መጫን ይችላሉ ፦
https://play.google.com/store/apps/details؟id=qissa.anbia.hudasoft

المزيد
تنزيل APK للاندرويد
تنزيل 30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ APK للاندرويد
1. انقر على "تنزيل 30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ APK للاندرويد"
2. تثبيت 30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ
3. تشغيل والاستمتاع بـ30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ
Google Play
تنزيل من متجر بلاي
1. انقر على "تنزيل من متجر بلاي"
2. تنزيل 30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ من متجر بلاي
3. تشغيل والاستمتاع بـ30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ
30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ APK FAQ

هل 30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ آمن لجهازي؟

المزيد

ما هو ملف XAPK، وماذا علي أن أفعل إذا كان ملف 30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ الذي قمت بتنزيله هو ملف XAPK؟

المزيد

هل يمكنني تشغيل 30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ على جهاز الكمبيوتر الخاص بي؟

المزيد

عمليات البحث الأكثر شيوعًا